የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የናይጄሪያው ኤር ፒስ የአፍሪካን የአቪዬሽን ትስስር የሚያጠናክር የጋራ የበረራ ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የናይጄሪያው ኤር ፒስ የአፍሪካን የአቪዬሽን ትስስር የሚያጠናክር የጋራ የበረራ ስምምነት ተፈራረሙ
ሁለቱ አየር መንገዶች በመላው አፍሪካ እና ባሻገር ያሉ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መስመሮችን የሚያስተሳስር የሁለትዮሽ የጋራ የበረራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሠረት ይህ አጋርነት፦
ተጓዦች በአንድ የጉዞ ትኬት ብቻ እና የሻንጣ ምዝገባ ሳይደጋገምባቸው እንዲንቀሳቀሱ ያስችላል።
ተሳፋሪዎች ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ወደ ናይጄሪያ እንዲሁም ከናይጄሪያ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያለ እንግልት በቀጥታ መጓዝ ይችላሉ።
አጋርነቱ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ውስጥ የሚደረገውን የሰዎች፣ የእቃዎችና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ሲሆን የቀጣናውን የቱሪዝም ዘርፍም ያነቃቃዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
