ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች* ቡድንን በቋሚነት በአሸባሪነት ፈረጀች
18:10 10.11.2026 (የተሻሻለ: 18:14 10.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች* ቡድንን በቋሚነት በአሸባሪነት ፈረጀች
የአሸባሪ አካላት እና አሸባሪዎች መዝገብ አስተዳደር ቢሮ ያስተላለፈው ይህ ውሳኔ፤ የመጨረሻ እና ይግባኝ የሌለው የፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ ሦስት ግለሰቦችንም በአሸባሪነት ፈርጇል።
ይህ ቋሚ ውሳኔ፣ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ የታገደ እና እንቅስቃሴዎቹም የተከለከሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
በግብፅ ሕግ መሠረት የቡድኑ ሀብትና ንብረት ይታገዳል፤ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው፤ ቢሮዎቹም መዘጋት አለባቸው። የቡድኑ አባል መሆን፣ ማስተዋወቅ እና አባል እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረብ በሕግ የተከለከለ ነው።
በአሸባሪነት የተፈረጁት ግለሰቦች የጉዞ እገዳ፣ የሀብት እገዳ እና የመንግሥት ወይም የምርጫ ኃላፊነት እንዳይይዙ መከልከልን ጨምሮ ሌሎች ሕጋዊ እርምጃዎች ይጠብቋቸዋል።
ይህ በቋሚነት የተሰጠ ፍረጃ ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የተሰጡ ጊዜያዊ ውሳኔዎችን የሚተካ ሲሆን፤ የመጨረሻው የጊዜ ገደብ ውሳኔ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2025 የሽብርተኝነት ፍረጃውን ለተጨማሪ አምስት ዓመታት አራዝሞት ነበር።
*በሩሲያም በአሸባሪ ድርጅትነት የተፈረጀ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
