በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕድገት የተደገፈው የቻይና የንግድ ትርፍ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ተሻገረ
17:25 10.11.2026 (የተሻሻለ: 17:34 10.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕድገት የተደገፈው የቻይና የንግድ ትርፍ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ተሻገረ
የቻይና የጉምሩክ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በጥቅምት ወር የሀገሪቱ የወጭ ንግድ ካፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በሁለት አኃዝ (35.2%) ያደገ ሲሆን፤ ይህም ቀደም ሲል ይገመታል ተብሎ ከነበረው 33.5% የገበያ ግምት በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።
የቻይና የንግድ ትርፍ እ.ኤ.አ. በ2026 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት ውስጥ 1.04 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፤ ይህም በተከታታይ ለሁለተኛ ዓመት የ1 ትሪሊዮን ዶላር ወሰንን ያለፈበት እና እ.ኤ.አ. ከ2025 ጋር ሲነጻጸር ከአንድ ወር ቀድሞ የተመዘገበ ስኬት ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ፉክክር ለቻይና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ፍላጎት የፈጠረ ሲሆን፤ ይህም የወጭ ንግዱን እ.ኤ.አ. እስከ 2027 ድረስ ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል።
በወጭ ንግድ መሪነት በሚመራው የኢኮኖሚ እድገት ሞዴል ውስጥ የቻይና መኪና ወጭ ንግድም ጠንካራ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
