የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 1 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ
15:45 10.11.2026 (የተሻሻለ: 15:54 10.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 1 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ
ኮርፖሬሽኑ በ2019 በጀት ዓመት ይህን ግብ ለማሳካት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ እስከ 2023 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ለኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 1 በመቶ ድርሻ የማበርከት ታላቅ ስትራቴጂያዊ ግብ አስቀምጧል።
አምስቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፦
🟠 ብቃት ያላቸውን ኢንቨስተሮች መሳብና ማቆየት፤
🟠 የፋይናንስ ዘላቂነትንና ትርፋማነትን ማረጋገጥ፤
🟠 በሁሉም ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የአሠራር ብቃትን ማሳደግ፤
🟠 ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶችን ማቅረብ፤
🟠 ተቋማዊ የአፈጻጸም አቅምን ማጎልበት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
