ዚምባብዌ ከሩሲያው ኩባንያ መድኃኒቶችን ለማስገባት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ ከሩሲያው ኩባንያ መድኃኒቶችን ለማስገባት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

የዚምባብዌ ሁለተኛው ምክትል ፕሬዝዳንት ኬምቦ ሞሃዲ የሁለቱን ሀገራት የሕክምና ዘርፍ የንግድ ትስስር ለማጠናከር በሴንት ፒተርስበርግ የሚገኘውን ፋርማሲንቴዝ-ኖርድ የተሰኘውን ግዙፍ የሩሲያ የፋርማሲዩቲካል ኩባንያ መጎብኘታቸውን የከተማዋ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ በመግለጫው አስታውቋል።

የሴንት ፒተርስበርግ ምክትል ገዥ ኪሪል ፖሊያኮቭ በማኅበራዊ ድረ-ገጻቸው፣ "ድርጅቱ ከሁለት ደርዘን በላይ የሆኑ የመድኃኒት ዓይነቶችን ወደ ዚምባብዌ ለመላክ ዝግጁ ነው" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን፤ ትኩረቱም በተለይም የካንሰር ሕክምና መድኃኒቶችን በማቅረብ ላይ እንደሆነ አክለዋል።

እንደ በጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል፣ ሴንት ፒተርስበርግ ከ4,000 በላይ የኢንሱሊን ካርትሪጆችን ለዚምባብዌ በድጋፍ መስጠቷን ኮሚቴው ጠቁሟል።

የአፍሪካን ገበያ አቅም ያጎላው ፋርማሲንቴዝ-ኖርድ ኩባንያ፤ በሰሜን እና በመካካለኛው አፍሪካ ያለውን አሁናዊ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ ወደ አኅጉሪቱ የሚደረገውን የመድኃኒት ወጭ ንግድ ለማስፋፋት የሚያስችል ማዕቀፍ ስምምነት ለመፈረም ማቀዱን አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0