የራስን ታሪክ መንገር፦ የአፍሪካ መገናኛ ብዙኃን የራሳቸውን ታሪክ እንዴት መተረክ ይችላሉ? - የኒጄራዊ የሕግ ባለሙያ ማብራሪያ
14:45 10.11.2026 (የተሻሻለ: 14:54 10.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የራስን ታሪክ መንገር፦ የአፍሪካ መገናኛ ብዙኃን የራሳቸውን ታሪክ እንዴት መተረክ ይችላሉ? - የኒጄራዊ የሕግ ባለሙያ ማብራሪያ
የሕግ ባለሙያው ኢብራሂማ ሳሉ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፤ የአፍሪካ መገናኛ ብዙኃን የዕለት ተዕለት የዜና ትረካዎቻቸውን ባለቤትነት ሙሉ በሙሉ በእጃቸው ለማድረግ የሚያስችሏቸውን ሦስት ዋና ዋና እርምጃዎች ዘርዝረዋል፡፡
1⃣ ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂ፦ በአፍሪካውያን መሪነት የሚካሄደውን ትርክት ለማስፋፋት እና ይህንን ጥረት የሚመሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ለመደገፍ የሚያስችል የተቀናጀ አቀራረብን መቅረጽ።
2⃣ የአስተሳሰብ ሽግግር፦ ህዝቡ የአፍሪካ ሀገር በቀል ይዘቶችን እና መረጃዎችን በንቃት እንዲከታተል የማኅበረሰቡን አስተሳሰብ መለወጥ።
3⃣ ዘላቂ የፋይናንስ አቅም፦ ለመሳሪያዎች ግዢ ብቻ ሳይሆን፤ ጋዜጠኞች ምርመራዎችን እንዲያካሂዱ እና መረጃዎችን በሰፊው እንዲያሰራጩ የሚያስችላቸውን አቅም ለመገንባት የሚያስፈልጉ ሀብቶችን ማረጋገጥ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
