በየዓመቱ 200 ያህል ኢትዮጵያውያን በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የነጻ ትምህርት እድል ተጠቃሚ እየሆኑ ነው - የማዕከል ዋና ዳይሬክተር
14:15 10.11.2026 (የተሻሻለ: 17:04 10.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በየዓመቱ 200 ያህል ኢትዮጵያውያን በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የነጻ ትምህርት እድል ተጠቃሚ እየሆኑ ነው - የማዕከል ዋና ዳይሬክተር
የሩሲያ መንግሥት በየዓመቱ ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ 200 የሚጠጉ የትምህርት ዕድሎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ በአዲስ አበባ የሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የግብርና ፈጠራ ዐውደ–ርዕይ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ ከፍተኛ አማካሪ አሌክሲ ቼስኖኮቭ በበኩላቸው፣ ዝግጅቱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በግብርና ዘርፍ ያላቸውን የፈጠራ ፍላጎት እና ህልም ከተግባራዊ እድል ጋር የሚያስተሳስሩበትን እድል የሚፈጥር መሆኑንማስረዳታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
“ሩሲያከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት እና የኢኮኖሚ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ቁርጠኛ ናት። ለአጋሮቻችን የምግብ ዋስትና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። በመሆኑም የሩሲያ የትምህርት ተቋማት ይህንን ፈተና ለመወጣት የሚያስፈልገውን ሳይንሳዊ ድጋፍ መስጠታቸውን ይቀጥላሉ፡፡” ሲሉ ቃል ገብተዋል።
በአስትራክሃን ታቲሽቼቭ ዩኒቨርሲቲ እና በሩሲያ የሰብአዊ ትብብር ኤጀንሲ የተዘጋጀው የግብርና ፈጠራ ዐውደ–ርዕይ፣ ከ500 በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችንና ባለሙያዎችን ከሩሲያ ዘመናዊ ግብርና ጋር ለማስተዋወቅ እና ነፃ የትምህርት እድል ለማመቻቸት ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
