- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ፍልሚያ፣ የዓለም አቀፉ የወንጀሎች ፍ/ቤት ኢፍትሃዊ ሥርዓት

የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ፍልሚያ፣ የዓለም አቀፉ የወንጀሎች ፍ/ቤት ኢፍትሃዊ ሥርዓት
ሰብስክራይብ

የውጭ ኩባንያዎች እና የውጭ መንግስታት በዘረመል የተሻሻሉ ሰብሎችን በዋናነት ይቆጣጠራሉ። በእነሱ ቁጥጥር ስር ናቸው። ምናልባት በነጻ ይሰጡናል ማለት ትችል ይሆናል። አንዴ መጠቀም ከጀመርክ በኋላ ግን፣ በብዙ ሌሎች ሀገራት ዘንድ እንዳየነው፣ የእነዚህ ሰብሎች ምርታማነት ይቀንሳል፣ በአካባቢያዊ ስነ-ምህዳር፣ በነፍሳት፣ እንስሳት እና በሌሎችም ይጠቃሉ። [...] የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች በአፍሪካ ድህነትን አልቀነሱም፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን አላጠፉም፣ የገበሬዎችንም ገቢ አልጨመሩም። ያደረጉት ነገር በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ወሳኝ፣ ወሳኝ ምግቦችን መተካት ወይም መቀነስ ነው።”

ሲሉ በአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ህብረት /AFSA/ ዋና አስተባባሪ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የአፍሪካ ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ ምዕራባውያን እና ኩባኒያዎቻቸው በአፍሪካ ላይ ለመተግበር ስለሚሞክሩት የምግብ ቅኝ ገዛት እና የአፍሪካን ትግል በአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ህብረት /AFSA/ ዋና አስተባባሪ ከሆኑት ከሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ጋር የምንቃኘው ሲሆን፤

በክፍል ሁለት፦ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኢፍትሃዊ እና ለምዕራባውያን ያደላውን አሰራር በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሶሺዮአንትሮፖሎጂስት እና መምህር ከሆኑት ከአቶ መሀመድ አወል ሀጎስ ጋር የምንቃኘው ይሆናል፡፡

🔊 ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ:
Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0