ግብፅ በዓባይ ወንዝና በቀይ ባሕር ዙሪያ በኢትዮጵያ ላይ የምትፈጥረው ማደናቀፍ አሁን ላይ ዋጋ አጥቷል - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ግብፅ በዓባይ ወንዝና በቀይ ባሕር ዙሪያ በኢትዮጵያ ላይ የምትፈጥረው ማደናቀፍ አሁን ላይ ዋጋ አጥቷል - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ከሀገር ውስጥ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፤ ግብፅ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና ኢትዮጵያን ከቀይ ባሕር የመነጠል ታሪካዊ አካሄዷ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ "የማይሰራ" መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።

የካይሮ "የውሃ መጠን ይቀንሳል" ስጋት በተግባር ውድቅ ሆኗል፤ ውሃው ተርባይኖችን አሽከርክሮ ወደ ታችኞቹ ሀገራት (ሱዳንና ግብፅ) መፍሰሱን የቀጠለ ሲሆን፣ በአረንጓዴ አሻራ ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው የውሃ ተፋሰሱን ጠብቆታል" ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለናይል ወንዙ አጠቃላይ የውሃ ፍሰት 86% የምታበረክት ቢሆንም፣ ግብፅ የውሃ ሀብቷን እንዳትጠቀም ለማገድ ስትሞክር መክረሟን የገለፁት ሚኒስትሩ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መገንባቱ እና ሥራ መጀመሩ ያንን አካሄድ በብቃት ለውጦታል ብለዋል።

“ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ በመገንባት ያንን የአስተሳሰብ መስመር መስበር ችላለች፤ ያንን ምዕራፍ ዘግተነዋል፡፡”

ግብፅ የራሷን የቶሽካና ኒው ቫሊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ያለ የላይኞቹ ሀገራት ፈቃድ ስትገነባ የነበረ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ግን ከሕዳሴው ግድብ ለኬንያ እና ጂቡቲ ኤሌክትሪክ በማቅረብ፣ ለሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ደግሞ ለማቅረብ በመሥራት የጋራ ብልጽግናን እያረጋገጠች ነው ሲሉ የካይሮን አቋም ኮንነዋል።

"ግብፅ በቀይ ባሕር መብት አላችሁ እያለች ኢትዮጵያ ግን የባሕር በር አልባ ሆና እንድትቀር መጠበቋ አያስማማም" ያሉት ሚኒስትሩ፣ ግብፅ የቀደመውን በብቸኝነት የመቆጣጠር ፍላጎቷን ትታ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንድትሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ከዚህ ቀደም በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፤ የቀይ ባሕር ደኅንነትና አስተዳደር በሕግም ሆነ በጂኦፖለቲካዊ እውነታ የቀይ ባሕር ዳርቻ ሀገራት ብቻ መብትና ኃላፊነት መሆኑን እና ኢትዮጵያ በዚሁ ማዕቀፍ ውስጥ እንድትሳተፍ የቀረበውን ፍላጎት ካይሮ እንደማትቀበለው አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0