- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ከፋሺዝም ውድቀት እስከ ኢትዮጵያ ድል አድራጊነት፡ የዛሬው ዓለም የጽንፈኝነት አዙሪት

ከፋሺዝም ውድቀት እስከ ኢትዮጵያ ድል አድራጊነት፡ የዛሬው ዓለም የጽንፈኝነት አዙሪት
ሰብስክራይብ
በየዓመቱ እ.ኤ.አ ህዳር 09 የጸረ-ፋሺዝም እና ፀረ-ሴማዊነት ቀን ይከበራል፤ እለቱ የጽንፈኝነት አደጋዎችን በማስታወስ ሰብዓዊ መብቶችን እና መቻቻልን ለመጠበቅ እለቱ በዓለምአቀፍ ደረጃ ይታሰባል።

እ.ኤ.አ. በ1935 ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረበት ወቅት፣ የኢትዮጵያውያን የነፃነት ትግል በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ የፀረ ፋሺዝምና የፀረ ቅኝ ግዛት ትግሎች ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ይዟል።

“የአውሮፓ ኃይሎች በወቅቱ ወደ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ባደረጓቸው ጉዞዎች በአካባቢዎቹ የነበሩ ማህበረሰቦች ላይ ያነጣጠሩ ስልታዊ የመፈናቀል እና የማጥፋት ሂደቶች እንደተፈጸሙ ይነሳል። እንዲሁም አፍሪካን በተመለከተ በተደረጉ ስብሰባዎችና ውሳኔዎች ላይ ተመሳሳይ ፖሊሲዎች እንደነበሩ ይብራራል” ሲሉ ኢትዮጵያዊው የታሪክ ባለሙያ እና ጸሐፊ ጥላሁን ጣሰው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ዛሬ በድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ የፋሺዝም፣ የዘረኝነትና የጥላቻ አስተሳሰቦችን በመቃወም የሚከበረውን ዓለም አቀፍ ቀን አስመልክተን፣ ኢትዮጵያ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ያሳየችውን የነፃነትና የክብር ትግል፣ ይህ ታሪካዊ ተሞክሮ በዓለም አቀፍ የፀረ ቅኝ ግዛትና የፀረ ጭቆና ንቅናቄዎች ላይ የነበረውን ተፅዕኖ፣ እንዲሁም ዛሬም በዓለም የሚታዩትን የጥላቻ፣ የመድልዎና የጽንፈኝነት አዝማሚያዎች ከታሪክ በምን መማር እንደምንችል ከታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ ከአቶ ጥላሁን ጣሰው ጋር እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0