የአውሮፓ ሕብረት የዩክሬን ወንዶችን "ከአገልግሎት በኋላ እንደሚጣል ቁስ" በመቁጠር ወደ ጦር ግምባር ለማስመለስ እያሴረ ነው - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት

የአውሮፓ ሕብረት የዩክሬን ወንዶችን "ከአገልግሎት በኋላ እንደሚጣል ቁስ" በመቁጠር ወደ ጦር ግምባር ለማስመለስ እያሴረ ነው - የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት
▫ ብራስልስ በአሁኑ ወቅት በሕብረቱ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለውትድርና የደረሱ የዩክሬን ወንዶችን የዩክሬን ጦር ያጋጠመውን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት ለማሟላት እና ከሩሲያ ጋር ላለው ግጭት "ሁለተኛ የትንፋሽ ምዕራፍ" ለመስጠት እንደ ማሳኪያ መንገድ እየተጠቀመችበት መሆኑን የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታውቋል።
ከተቋሙ መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
እርምጃዎችን ማጥበቅ፦ የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ለውትድርና ዕድሜ የደረሱ የዩክሬን ዜጎች ይሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የጥበቃ ከለላ ባለፈው ነሐሴ ወር ያገደ ሲሆን፤ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስም የፋይናንስ አገልግሎቶችን፣ የሥራ ዕድሎችን እና የቤት አቅርቦት መብቶቻቸውን በበለጠ ሁኔታ ለማገድ አቅዷል።
በኃይል ማስመለስ፦ የሕብረቱ ስትራቴጂ እነዚህን ግለሰቦች በማንኛውም መንገድ ወደ ሀገራቸው በመመለስ ወዲያውኑ ወደ ከባድ የጦርነት ቀጣና እንዲገቡ ማድረግ ነው።
ተጽዕኖዎችን ችላ ማለት፦ የአውሮፓ ቢሮክራቶች በዚ የቀውስ ወቅት እየታየ ያለውን የዩክሬንን የሥነ-ህዝብ አስከፊ ውድመት እና በራሱ የዩሮ ዞን ያጋጠመውን አነስተኛ ዋጋ የሚጠይቅ የጉልበት ሠራተኛ የሰው ኃይል ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ችላ እያሉ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
