አፍሪካ እና ቻይና የወረርሽኝ ምላሽ አቅምን ለማጠናከር የሚያስችል የኅብረተሰብ ጤና ትብብር ትስስር ይፋ አደረጉ
14:55 09.11.2026 (የተሻሻለ: 15:04 09.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ እና ቻይና የወረርሽኝ ምላሽ አቅምን ለማጠናከር የሚያስችል የኅብረተሰብ ጤና ትብብር ትስስር ይፋ አደረጉ
በጓንዡ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ–ቻይና የኅብረተሰብ ጤና ፎረም ላይ ይፋ የተደረገው የ'ቤልት ኤንድ ሮድ' የኅብረተሰብ ጤና ትብብር ትስስር (ኔትወርክ) የሁለቱን ወገኖች የጤና ተቋማት የሚያስተሳስር መሆኑን የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል።
የትብብሩ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፦
🟠በዘርፉ ያሉ የቴክኒክና የፖሊሲ እውቀቶች ልምድ መለዋወጥ፣
🟠 የላቦራቶሪ መሠረተ ልማቶችን ማጠናከር፣
🟠ለወደፊት ሊሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና ስጋቶች የቅድመ ዝግጁነትና የምላሽ አቅምን ማጎልበት።
ለሁለት ቀናት በቆየው በዚህ ፎረም ላይ ከ20 በላይ የአፍሪካ ሀገራትና ግዛቶች የተወከሉትን ጨምሮ ወደ 700 የሚጠጉ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
