ሩሲያዊቷ ኤሊና ታሞኮቫ በዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ በቴኳንዶ የብር ሜዳሊያ አገኘች
13:15 09.11.2026 (የተሻሻለ: 13:24 09.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያዊቷ ኤሊና ታሞኮቫ በዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ በቴኳንዶ የብር ሜዳሊያ አገኘች
ሩሲያዊቷ አትሌት ኤሊና ታሞኮቫ እስከ 44 ኪሎ ግራም የክብደት ወሰን የቴኳንዶ የፍፃሜ ውድድር በክሮኤሽያዋ ፔትራ ኡግሌሲች በመሸነፏ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።
ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
🟠 ይህ ስኬት ቡድኑ ቀደም ሲል ካስመዘገባቸው ስድስት የወርቅ ሜዳሊያዎች በተጨማሪ ለሩሲያ በውድድሩ አምስተኛውን የብር ሜዳሊያ ያስገኘ ነው::
🟠 የሴኔጋል መዲና ዳካር 4ኛውን የወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር እያስተናገደች የምትገኝ ሲሆን፤ ይህም የኦሊምፒክ መድረክ በአፍሪካ አኅጉር ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው።
🟠 ውድድሩ እስከ ሕዳር 4 የሚቀጥል ሲሆን፤ በ25 የስፖርት ዓይነቶች 2700 ያህል አትሌቶች ይሳተፉበታል።
🟠 ሩሲያ በብሔራዊ አርማዎቻቸው ሥር በሚወዳደሩ 13 አትሌቶች ተወክላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
