በአቡ ዳቢ የሚደረጉ ድርድሮች ያለ አውሮፓውያን ተሳትፎ ለማካሄድ የታቀዱ ናቸው - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
12:40 09.11.2026 (የተሻሻለ: 13:04 09.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአቡ ዳቢ የሚደረጉ ድርድሮች ያለ አውሮፓውያን ተሳትፎ ለማካሄድ የታቀዱ ናቸው - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
በአሜሪካ አሸማጋይነት በሚካሄደው ድርድር ላይ ሩሲያ እና ዩክሬን ብቻ እንደሚሳተፉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል፡፡
በዲምትሪ ፔስኮች የተሰጡ ተጨማሪ መረጃዎች፦
🟠 ሩሲያ፣ አሜሪካ እና ቻይና በመሪዎቻቸው መካከል ሊካሄድ በሚችለው ስብሰባ አጀንዳ ላይ ሐሳብና ምልከታዎችን እየተለዋወጡ ሲሆን, መሪዎቹ ሰፋፊ አኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ሊወያዩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
🟠 በፑቲን፣ በትራምፕ እና በሺ ጂንፒንግ መካከል የሚደረገው ስብሰባ እጅግ ትኩረት የሚስብ እና የመላው ዓለም ዐይን ማዕከል እንደሚሆን ተገልጿል።
🟠 ከጂኦግራፊ አንጻር ዩክሬን በአሁኑ ወቅት በተግባር የተለየች ሀገር ሆናለች፤ በመሬት ላይ ያሉት እውነታዎችም ግልጽ መሆናቸው ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
