የኢትዮጵያ ዳኞች ለከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረትና ደኅንነት ሥጋት መጋለጣቸው አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ዳኞች ለከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረትና ደኅንነት ሥጋት መጋለጣቸው አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ዳኞች ለከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረትና ደኅንነት ሥጋት መጋለጣቸው አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.11.2026
ሰብስክራይብ

‍ የኢትዮጵያ ዳኞች ለከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረትና ደኅንነት ሥጋት መጋለጣቸው አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

 

በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የዳኞች አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ደኅንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የፌዴራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው ጥናታዊ ሲምፖዚየም ላይ የተገኙ የሕግ ባለሙያዎች፣ ዳኞችና ምሁራን ማስታወቃቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

 

ዋና ዋና የዘገባው ነጥቦች፦

 

ከባድ የሥራ ጫና፦ ዳኞች በመቶዎች የሚቆጠሩ መዝገቦችን በብቸኝነት የሚያዩ በመሆናቸው ለከፍተኛ የአካልና የአዕምሮ ጤና ቀውስ እየተዳረጉ ይገኛሉ።

 

የሕይወት መስዋዕትነት፦ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 4 ዳኞች በሥራ ጫናና በጤና እክል በሥራ ገበታቸው ላይ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ አንዲት ሴት ዳኛ ደግሞ በችሎት ላይ እያለች በጥይት ተገድላለች።

 

የሥነ-ልቦና ስብራት፦ በየዕለቱ የሚሰሟቸው አሰቃቂ ታሪኮች፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና ማኅበራዊ ጫናዎች ዳኞች ማስረጃ የመመዘንና ሕግ የመተርጎም ብቃታቸውን እየፈተነው ይገኛል።

 

የፖሊሲ እና የጥበቃ ክፍተት፦ የዳኞችን አካላዊና አዕምሯዊ ደኅንነት የሚያስጠብቅ "የዳኝነት ፖሊሲ" አለመኖሩና ለቤተሰቦቻቸው በቂ ጥበቃ አለመደረጉ ቀውሱን አባብሶታል።

 

የመፍትሔ ጥሪ፦ ችግሩ ከፍርድ ቤቶች አቅም በላይ በመሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፖሊሲ አውጭ አካላት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብተው የደኅንነት፣ የማኅበራዊ ዋስትና እና የአዕምሮ ጤና ፕሮግራሞችን በሕግ እንዲዘረጉ ጥሪ ቀርቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0