የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከፍተኛ አዛዥ አማፂ ቡድኑን በዘመድ አዝማድ አሠራር በመክሰስ የሱዳን ጦር ኃይልን ተቀላቀሉ
11:15 09.11.2026 (የተሻሻለ: 11:24 09.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከፍተኛ አዛዥ አማፂ ቡድኑን በዘመድ አዝማድ አሠራር በመክሰስ የሱዳን ጦር ኃይልን ተቀላቀሉ
በሱዳን የፈጣኖ ደራሽ ኃይሎች አማፂ ቡድን ውስጥ የ15ኛው ምድብ አዛዥ የሆኑት ሲዲቅ መሐመድ አብደልራሕማን አንደር ከ200 ተዋጊዎች እና ከ40 ያህል ተሽከርካሪዎች ጋር ወደ ሀገሪቱ መደበኛ የጦር ኃይሎች መቀላቀላቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።
አዛዡ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ የሆኑትን መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን (ሔመቲ) በዘመድ አዝማድ አሰራር የከሰሱ ሲሆን፣ ሔመቲ በአማፂ ቡድኑ ማዕረጎች ውስጥ ለራሳቸው ቤተሰብ አባላት ብቻ ቅድሚያ ይሰጣሉ ሲሉ ተናግረዋል።
"ይህንን የቡድኑ የአመራር አሰራር ለመቃወም የሚደፍሩ ሁሉ በእስራት ይቀጣሉ" ሲሉ አንደር በቪዲዮ መግለጫቸው አስታውቀዋል።
የዚህ አዛዥ ቡድኑን መተው በቅርብ ጊዜያት የታዩ ከፍተኛ አዛዦች ከቡድኑ የመልቀቅ ሂደት አካል ነው።
በቅርብ ወራት ውስጥ ሌሎች በርካታ መኮንኖች ቡድኑን በመልቀቅ ሀገራዊ ጦሩን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ ከእነሱም መካከል በቅርቡ ከ300 ተዋጊዎች ጋር ቡድኑን የለቀቁት መሐመድ አዝራቅ አል-ፈንጃሪ ይገኙበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
