ትራምፕ የኢራን ጦርነትን የማባባስ ፍላጎት እንደሌላቸው ገለፁ

ሰብስክራይብ

ትራምፕ የኢራን ጦርነትን የማባባስ ፍላጎት እንደሌላቸው ገለፁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአጋማሽ ዘመን ምርጫ መጠናቀቁን ተከትሎ ከኢራን ጋር ያለውን ግጭት የማባባስ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

አሜሪካ በስፍራው ያላትን ወታደራዊ ኑባሬ ላልተወሰነ ጊዜ ማቆየት እንደምትችል የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ "በጣም ውድ አይደለም፤ እዚያው ላልተወሰነ ጊዜ ልንተዋቸው እንችላለን" ሲሉ አክለዋል።

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አጋር ሀገራት ለአሜሪካ ሙሉ የጦርነት ወጪዋን እንደሚመልሱላት የነበራቸውን እምነት ዳግም አጽንኦት ሰጥተውበታል።

"ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ የጠበቅናቸው ሀገራት ለጦርነቱ ያወጣነውን ማንኛውንም እና ሁሉንም ወጪ ይከፍሉናል። ምክንያቱም ያለ እኛ ህልውና ሊኖራቸው አይችልም ነበር፤ ያለ እኛ እስራኤል ህልውና አይኖራትም ነበር" ሲሉ ለሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0