የሩሲያ ሳይንቲስቶች ባክቴሪያዎችን በመጠቀም የአፈርን ለምነት መገምገም የሚያስችል አዲስ መንገድ አገኙ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ሳይንቲስቶች ባክቴሪያዎችን በመጠቀም የአፈርን ለምነት መገምገም የሚያስችል አዲስ መንገድ አገኙ
የሩሲያ ሳይንቲስቶች ባክቴሪያዎችን በመጠቀም የአፈርን ለምነት መገምገም የሚያስችል አዲስ መንገድ አገኙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ሳይንቲስቶች ባክቴሪያዎችን በመጠቀም የአፈርን ለምነት መገምገም የሚያስችል አዲስ መንገድ አገኙ 

 

የሩሲያ ሩድን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሚታረስ መሬትን እውነተኛ የማምረት አቅም የሚወስነው በውስጡ ያለው የባክቴሪያ መጠን እንደሆነ ማረጋገጣቸውን የተቋሙ መግለጫ አመልክቷል። 

ባሕላዊ የእርሻ ልምዶች፣ አፈርን ሳይገለብጡ የሚካሄዱ እርሻዎች ወይም አፈር ሳይነካ የሚተገበሩ የምርት ዘዴዎችን ጨምሮየ ተለያዩ የእርሻ መንገዶች በረቂቅ ሕዋሳት ስብጥር ላይ ለውጥ ያመጣሉ። ይህም የአፈሩን ለተክሎች ንጥረ ምግብ የማቅረብ አቅም ይወስናሉ። 

 

"ለዕፅዋት ጠቃሚ ከሆኑ ተግባራት ጋር የተያያዙ የዘረመል ባህሪያትን ለመለየት የሚያስችል ዘዴ ፈጥረናል። እነዚህም የናይትሮጅንና የፎስፈረስ ልውውጥ ሂደቶችን እንዲሁም የዕፅዋት ሆርሞኖችን ማምረት ያካትታሉ" ሲሉ የዩኒቨርሲቲው የሥነ ምህዳር ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ አሌክሲ ቫትሊን ገልጸዋል። 

 

ይህ በባክቴሪያዎች ላይ የሚካሄድ ትንተና አርሶ አደሮች የዘር ወቅት ከመጀመሩ በፊት የአፈራቸውን ጥራት በትክክል ለመገምገም እንደሚያስችላቸው ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0