የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ታሪክ እንዲጠበቅና ተቋማዊ አቅሟ እንዲጠናከር ከምንግዜውም በላይ በትኩረት ይሠራል - መንግሥት

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ታሪክ እንዲጠበቅና ተቋማዊ አቅሟ እንዲጠናከር ከምንግዜውም በላይ በትኩረት ይሠራል - መንግሥት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ታሪክ እንዲጠበቅና ተቋማዊ አቅሟ እንዲጠናከር ከምንግዜውም በላይ በትኩረት ይሠራል - መንግሥት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ታሪክ እንዲጠበቅና ተቋማዊ አቅሟ እንዲጠናከር ከምንግዜውም በላይ በትኩረት ይሠራል - መንግሥት 

 

የሰላም ሚኒስትሩ ሙሳ አደም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች ጋር ባደረጉት ትውውቅ፤ መንግሥት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ከሐይማኖት ተቋማት ጋር የጀመረውን ገንቢ ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለቤተ-ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ መጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል። 

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው ቤተ-ክርስቲያኗ ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ እና ምዕመናን በሰላም ተግባራቸውን እንዲያከውኑ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል። 

 

የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላምን እውን ለማድረግ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን እና ከሌሎች የሐይማኖት ተቋማት ጋር የተጀመሩ የጋራ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል። 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0