የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግሥት ሠራተኞች የብቃትና የባህሪ መመዘኛ መመሪያዎችን ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግሥት ሠራተኞች የብቃትና የባህሪ መመዘኛ መመሪያዎችን ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው
ኮሚሽኑ በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 መሠረት የመንግሥት ሠራተኞችን በባህሪ፣ በክህሎት እና በአገልግሎት አሰጣጥ ለመመዘን የሚያስችሉ 18 አዳዲስ መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በመመሪያዎቹ ድንጋጌ መሠረት ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በያዘው የሥራ መደብ ላይ ለመቆየት፣ የደረጃ እድገት ለማግኘት፣ ከአንድ መሥሪያ ቤት ወደ ሌላ ለመዛወርም ሆነ በአዲስ ለመቀጠር የቴክኒካል እና የባህሪ ብቃት ምዘናዎችን አልፎ ማረጋገጫ ማግኘት ይጠበቅበታል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
አንድ ሠራተኛ በያዘው የሥራ መደብ ላይ ለመቀጠል በባህሪያዊ፣ በቴክኒካል እና በተግባር ምዘናዎች በእያንዳንዳቸው ቢያንስ 70% ውጤት የማምጣት ግዴታ አለበት።
በሦስቱም መመዘኛዎች ከ90% በላይ የሚያመጣ ሠራተኛ፤ የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይደረግለታል። ከ75% እስከ 90% የሚያመጣ ሠራተኛ የአንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ ያገኛል።
የባህሪ ምዘናው በዘልማድ አስተያየት ሳይሆን እንደ የቡድን ሥራ ፣ አርአያነት፣ ታዛዥነት እና የሥነ-ምግባር ሳይንሳዊ መስፈርቶች ላይ ተመስርቶ ይከናወናል።
እስከ ወረዳ ደረጃ ባሉ የሙያ መስኮች ምዘናውን ላለፈ ሠራተኛ የሚሰጠው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለ5 ዓመታት ያገለግላል።
በመጀመሪያው ዙር ፈተና ያላላለፈ ሠራተኛ ተቋሙ አዘጋጅቶ በ6 ወራት ውስጥ ድጋሚ የመፈተን ግዴታ አለበት።
አዲሱ አሠራር ሠራተኛ መቀነስ ሳይሆን ተልዕኮ የሚሸከም ብቁ ሠራተኛ የመገንባት ዓላማ እንዳለው ተመላክቷል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
