ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የያዘ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አገኘች
15:35 08.11.2026 (የተሻሻለ: 15:44 08.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የያዘ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አገኘች
ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር ባካሄደችው የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማግኘቷንና በፍጥነት ምርት ማውጣት ለመጀመር ማቀዷን የሀገሪቱ የፔትሮሊየም እና የማዕድን ሀብት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
የጋዝ ክምችት፦ 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ይዟል ተብሎ የተገመተ ሲሆን ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለውን የተጣራ መጠን ለመወሰን ጥናቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
አዲስ የማስተላለፋያ መስመር ፦ የጋዝ ማውጣት ሂደቱን ለማፋጠን የጋዝ ጉድጓዱን ከነባር የመሠረተ-ልማት አውታር ጋር የሚያገናኝ 22 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ታቅዷል።
ተጨማሪ የፍለጋ ሥራዎች፦ እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ ከሆነ የተሻሻሉ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች እና ያልተከፈሉ ውዝፍ ክፍያዎች ለአጋሮች መከፈላቸው ተጨማሪ የፍለጋ ሥራዎችን ለማካሄድ መነቃቃትን ፈጥሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
