ኬንያ በሞምባሳ ወደብ ግዙፍ የመርከብ ጥገና ማዕከል ልትገነባ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaኬንያ በሞምባሳ ወደብ ግዙፍ የመርከብ ጥገና ማዕከል ልትገነባ ነው
ኬንያ በሞምባሳ ወደብ ግዙፍ የመርከብ ጥገና ማዕከል ልትገነባ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2026
ሰብስክራይብ

ኬንያ በሞምባሳ ወደብ ግዙፍ የመርከብ ጥገና ማዕከል ልትገነባ ነው 

 

በመንግሥት ባለቤትነት የሚደዳደረው ኬንያ ሺፕያርድስ ሊሚትድ፤ ሥራውን ለማስፋፋት እና ከሕንድ ውቅያኖስ የገበያ ዕድል ለመጠቀም ለግዙፍ ዓለም አቀፍ መርከቦች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ልዩ የመርከብ ማቆሚያ እና ጥገና ማዕከል በሞምባሳ ወደብ ለመገንባት ማቀዱን ይፋ አድርጓል። 

 

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦ 

 

◾ የማዕከሉ አቅም፦ አዲሱ የመርከብ ጥገና ማዕከል ከ185 እስከ 285 ሜትር ርዝመት ያላቸውን መርከቦች ማስተናገድ የሚችል ሲሆን በዓመት እስከ 32 የመርከብ ጥገና ውሎችን የማከናወን አቅም ይኖረዋል። 

 

◾ የገበያ ፍላጎት፦ በቅርቡ ለፓርላማ የቀረበው ይህ የፕሮጀክት ሀሳብ፤ በአሁኑ ወቅት በሕንድ ውቅያኖስ ቀጣና በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ዘንድ የሚታየውን የመርከብ ጥገና ማዕከላት እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው። 

 

◾ የሀገር ውስጥ አቅም፦ እ.ኤ.አ በ2020 የተቋቋመው ኬኤስኤል የሀገር ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ አቅሙን እያሰፋ የሚገኝ ሲሆን 100 ሜትር ርዝመት ያላትን 'ኤምቪ ኡሁሩ 2' የተሰኘችውን የጭነት መርከብ በስኬት ገንብቶ ማጠናቀቁ ይታወሳል። 

 

◾ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ትስስር፦ ተቋሙ የሮቦቲክ ብየዳ ሥርዓቶችን ጨምሮ የላቁ ቴክኖሎጂዎችን የያዘ ሲሆን የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ወጪ በድርድር ከ5.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ 2.8 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማድረግ ችሏል። 

 

◾ ዐውድ፦ ማስፋፊያው የሞምባሳ ወደብ በዓለም ባንክ የ2024 ግምገማ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ አፈፃፀም ካላቸው ወደቦች ከተመደበ በኋላ የመጣ ነው። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0