ሩሲያ የዩክሬንን የሚሳኤል ምርት አቅም አሽመድምዳለች - ባለሙያ
12:47 08.11.2026 (የተሻሻለ: 12:54 08.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ የዩክሬንን የሚሳኤል ምርት አቅም አሽመድምዳለች - ባለሙያ
የሩሲያ ኃይሎች ፍላሚንጎ የተሰኙትን ክሩዝ ሚሳኤሎች በሚያመርተው ዚቶሚር ፋብሪካ ያደረሱት ጥቃት "የዩክሬንን የጦር መሣሪያ ምርት አቅም አሳጥቷል" ሲሉ የወታደራዊ ተንታኝ እና የቀድሞው የሩሲያ ጦር ኮሎኔል ቪክቶር ሊቶቭኪን ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
"ዩክሬን ፍላሚንጎ ሚሳኤሎችን ማምረት ካልቻለች፤ ቮሮኔዝ፣ ቤልጎሮድ፣ ኩርስክ እና ሞስኮን ጨምሮ በዋና ዋና የሩሲያ ከተሞች ላይ ሚሳኤሎቹን ማስወንጨፍ አትችልም" ሲሉ አክለዋል።
የሩሲያ ጦር ለሮኬት ነዳጅ የሚሆኑ ግብዓቶችን የሚያመርተውን የብሮቫሪ ፖውደር የብረታ ብረት ፋብሪካን ማውደማቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የጠቀሱት ሊቶቭኪን፤ ሩሲያ መሰል ተቋማት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ወደፊት ሊሰነዘሩ የሚችሉ የዩክሬን ሚሳኤል ጥቃቶችን አስቀድማ መከላከል መቻሏን አስምረውበታል።
በተጨማሪም የዩክሬን የአየር መከላከያ ሥርዓቶች በኪየቭ ክልል የሚገኘውን የትሪፖልስካያ የሙቀት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከጥቃት መከላከል እንዳልቻሉም ጠቁመዋል።
የምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን ያቀረቧቸው የፓትሪዮት እና አይሪስ-ቲ መከላከያዎች እንደ ኪንዛል፣ ዚርኮን፣ ኦኒክስ እና ኢስካንደር ያሉትን የሩሲያ የሃይፐርሶኒክ፣ ሱፐርሶኒክ እና ባሊስቲክ ሚሳኤሎች የማክሸፍ አቅም የላቸውም ሲሉ ባለሙያው ድምዳሜያቸውን ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
