በፖላንድ ክራኮው ታሪካዊ ማዕከል በተፈጸመ ጥቃት የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
በፖላንድ ክራኮው ታሪካዊ ማዕከል በተፈጸመ ጥቃት የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
ቅዳሜ ዕለት በክራኮው ዋና አደባባይ ወታደራዊ ልብስ ያደረገ የ24 ዓመት ፖላንዳዊ በአላፊ አግዳሚው ላይ ተኩስ ከፍቷል፡፡
እስካሁን የተረጋገጡ ዝርዝር መረጃዎች፦
ጥቃቱ፦ ወታደራዊ ልብስ ያደረገው ተኳሽ ከቀኑ 09:00 ገደማ ታርጋ ከሌለው ሱባሩ መኪና ውስጥ በጦር መሣሪያ ተኩስ ከፍቷል። ፖሊስ በመኪናው ውስጥ በርካታ የጦር መሣሪያዎችን እና ጥይቶችን አግኝቷል።
የጉዳት መጠን፦ በወንጀሉ የ6 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን (አራት ሴቶች እና ሁለት ወንዶች፣ አንዱ የብሪታንያ ዜጋ ነው)፤ ሁለት የፖሊስ አባላት እና አምስት የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ 15 ሰዎች ቆስለዋል (የ12ቱ ሁኔታ አሳሳቢ ነው)።
ተኳሹ፦ ግለሰቡ በፖሊስ ጥይት ከተመታ እና ከተጎዳ በኋላ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ተጨማሪ ግኝት፦ ባለሥልጣናት በተኳሹ መኖሪያ ቤት ውስጥ የ3 ሰዎች አስከሬን ያገኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ የቤተሰብ አባላት ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ገልጸዋል።
የለሊቱ ክስተት፦ ፖሊስ ለሊት 09:00 ገደማ ቢላዋ የያዘ የ23 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ስር አውሏል። የፖሊስ አባላት በተኮሱት ጥይት ተመቶ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ክስተቱ ከአደባባዩ ጥቃት ጋር ግንኙነት እንደሌለው ታመኗል።
ብሔራዊ የሐዘን ቀን፦ ፕሬዚዳንት ካሮል ናቭሮትስኪ ከእሁድ ጀምሮ የሁለት ቀን ብሔራዊ የሐዘን ጊዜ አውጀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
