የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ሽግግርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ያፋጥናል ያሉትን የ 'አዲስ አበባ መግለጫ' አጸደቁ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ሽግግርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ያፋጥናል ያሉትን የ 'አዲስ አበባ መግለጫ' አጸደቁ 

 

በአዲስ አበባ በተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ 'አኅጉራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማፋጠን፣ ሕገ-መንግሥታዊ አስተዳደርን ለማጠናከር እና ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት ያስችላል' የተባለው የአዲስ አበባ መግለጫ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ጸድቋል። 

 

መግለጫው የፖለቲካ ፓርቲዎች አኅጉሪቷን ወደተሻለ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እና የተረጋጋ ፖለቲካ ለመምራት የሚያስችሏቸውን ቁልፍ አቅጣጫዎች አስቀምጧል።  

 

የመግለጫው ቁልፍ ትኩረቶች፦ 

 

ፓርቲዎቹ የሕግ የበላይነት፣ ፖለቲካዊ ብዝሃነት እና ሰላማዊ የፖለቲካ ውድድርን ለማስከበር ቁርጠኝነታቸውን የገለጹ ሲሆን ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆኑ የሥልጣን ለውጦችን በጽኑ አውግዘዋል።  

 

በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርናና ማዕድን ማቀናበር እና በዲጂታል ኢንዱስትሪዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በሀገር ውስጥ እሴት መጨመርን ማጠናከር እንዲሁም ሀገራት በተፈጥሮ ሀብቶቻቸው ላይ ያላቸውን ሉዓላዊ መብት ማረጋገጥ እንደሚገባ አስረግጠዋል። 

 

በሀገር ውስጥ ፋይናንስ በማሰባሰብ፣ የካፒታል ገበያዎችን ማጠናከር እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ግቦችን በማሳካት አኅጉራዊ የንግድ ትስስርን ማሳደግ እንደሚገባ ተነስቷል። 

 

የወጣቶችና የሴቶችን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ውሳኔ ሰጪነት ማረጋገጥ እና የወጣቶች የፖለቲካ ፎረምን ማጠናከር ይገባል ተብሏል። 

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የአመራር ሥልጠና ዕድሎች ለአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ለማድረግ የገቡትን ቃል መግለጫው በደስታ ተቀብሎታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0