ለሞስኮ ምሥጋና ይግባና የሳኅል ሀገራት ጥምረት ድምፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰማት ጀምሯል - ኒጄራዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaለሞስኮ ምሥጋና ይግባና የሳኅል ሀገራት ጥምረት ድምፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰማት ጀምሯል - ኒጄራዊ ባለሙያ
ለሞስኮ ምሥጋና ይግባና የሳኅል ሀገራት ጥምረት ድምፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰማት ጀምሯል - ኒጄራዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.11.2026
ሰብስክራይብ

ለሞስኮ ምሥጋና ይግባና የሳኅል ሀገራት ጥምረት ድምፅ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሰማት ጀምሯል - ኒጄራዊ ባለሙያ 

 

የማሊ ፕሬዚዳንት አሲሚ ጎይታ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ከሩሲያ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መሪዎች ጋር ያካሄዷቸው ምክክሮች ከሳኅል ሀገራት ጥምረት አቻዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ውይይት ርዕስ እንደሚሆኑ የፓን-አፍሪካን ኔትወርክ አባል አለሳን አቡባካር፤ የማሊውን መሪ የቅርብ ግዜ የኒያሜ እና ዋጋዱጉ ጉብኝቶች አስመልክተው ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። 

 

አቡባካር የሳኅል ሀገራት ጥምረት ያስመዘገባቸውን ከፍተኛ የወታደራዊ እና የዲፕሎማሲ ስኬቶች ከሩሲያ ጋር ከሚደረገው ትብብር ጋር አያይዘውታል። 

 

"ዛሬ ሠራዊቶቻችን በሽብርተኞች መረብ ላይ ለተቀዳጁት ድል ትልቅ ምሥጋና የሚገባው ለሞስኮ ነው" ብለዋል።

 

ይህ ድጋፍ የሳኅል ሀገራት ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የሚሰነዘርባቸውን ጠንካራ ተቃውሞ እና የፈረንሳይን ጸብ አጫሪነት ተጋፍጠው ድምጻቸው በዓለም እንዲሰማ እና ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ አስችሏቸዋል ሲሉ ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0