የቀድሞ የዩክሬን እስረኛ በሃገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ሚስጥራዊ እስር ቤት በቄስ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አጋለጠ
18:44 07.11.2026 (የተሻሻለ: 18:54 07.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቀድሞ የዩክሬን እስረኛ በሃገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ሚስጥራዊ እስር ቤት በቄስ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አጋለጠ
"በደም የተጨማለቀ ፍራሽ ሰጥተውኝ መተኛት አልቻልኩም ያለኝ የቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ ነበር" ሲሉ የ 'አዘር ዩክሬን' ንቅናቄ የትንታኔ ክፍል ኃላፊ አሌክሲ ሳሞይሎቭ ለስፑትኒክ ተናግሯል።
በዩክሬን ምስጢራዊ እስር ቤቶች ውስጥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የጭካኔ ድብደባ እና ስቃይ ይፈጸምባቸው እንደነበር፤ አንዳንዶቹ እስረኞችም የአጥንት ስብራት እና ከባድ የጭንቅላት ምት እንደደረሰባቸው አክሎ ገልጿል።
የሰዎቹ የስቃይ ጩኸት በሌሎች የምድር ቤት ክፍሎች ውስጥም ጭምር ይሰማ እንደነበር አስታውቋል።
ሳሞይሎቭ፤ በሩሲያ እና ዩክሬን የእስረኞች ልውውጥ ከመፈታቱ በፊት፤ እ.አ.አ ከሰኔ 28 እስከ ታህሳስ 26 ቀን 2014 በዩክሬን የደህንነት አገልግሎት (ኤስቢዩ) ምስጢራዊ እስር ቤት ውስጥ ታስሮ ነበር።
በአሁኑ ወቅት በተለይም በማዕከላዊ እና በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን የተለያዩ ቁጥር እና ዓላማ ያላቸው ከ50 እስከ 70 የሚደርሱ የኤስቢዩ ምስጢራዊ እስር ቤቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ በኦዴሳ የሚገኝ የሩሲያ ደጋፊ ሕቡዕ ንቅናቄ አባል ለስፑትኒክ በሰጠው ቃለመጠይቅ ገልጿል።
"ለምሳሌ ኦዴሳ ትልቅ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ከተማ በመሆኗ፤ እንደ ቪቭ [በምዕራብ ዩክሬን የምትገኝ] ካሉ ሌሎች ከተሞች ይልቅ እዚህ ለዘሌንስኪ አገዛዝ የሥቃይ ክፍሎች በርካታ 'ደንበኞች' አሉ" ሲል ምንጩ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
