የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ ዘርፍ የ15% ዕድገት በማስመዝገብ 878 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገባ
18:08 07.11.2026 (የተሻሻለ: 18:14 07.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ ዘርፍ የ15% ዕድገት በማስመዝገብ 878 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገባ
ገቢው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከ131 ሺህ 069 ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በመላክ እንደተገኘ ተገልጿል።
ከፍተኛ ቡና የተላከባቸው ቀዳሚ ሀገራት፦
ሳዑዲ አረቢያ፦ በመጠን 28,362.77 ቶን (22%)፤ በገቢ 196.85 ሚሊዮን ዶላር (22%)፣
ጀርመን፦ በመጠን 22,924.18 ቶን (17%)፤ በገቢ 136.69 ሚሊዮን ዶላር (16%)፣
ቻይና፦ በመጠን 15,125.54 ቶን (12%)፤ በገቢ 103.0 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (12%)።
ሩሲያ 10ኛዋ የኢትዮጵያ ቡና ገዢ ሀገር መሆን እንደቻለች የተገለጸ ሲሆን ከዋና ዋና መዳረሻዎቹ የተገኘው ገቢ ከ2018 ዓ.ም ጋር ሲወዳደር የ19% ጭማሪ ማሳየቱን የቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
