ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ዕቅድ ወደ ትግበራ አስገባች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ዕቅድ ወደ ትግበራ አስገባች
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ዕቅድ ወደ ትግበራ አስገባች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.11.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ዕቅድ ወደ ትግበራ አስገባች 

 

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዕቅዱ “የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤን ማጠናከር፣ የዲጂታል ጤና ሥርዓትን ማሳደግ፣ የድንገተኛ አደጋ ምላሽን ማጠናከርና የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነት ማስፋት ላይ ያተኩራል” ብለዋል። 

 

የዕቅዱ ሌሎች ቁልፍ ትኩረቶች፦ 

የሕፃናት ሞትን መቀነስ፣  

ወባ፣ ሳንባ ነቀርሳና ኤችአይቪን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎችን መከላከልና መግታት፣ 

የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችና የአዕምሮ ጤና አገልግሎቶችን ማስፋት፣ 

የስፔሻሊቲና ሱፐር ስፔሻሊቲ ሕክምናዎችን፣ የደምና የመድኃኒት አቅርቦትን ማሻሻል፣  

በግጭት የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ መገንባት። 

 

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ በራሷ ሀብት፣ ባለሙያዎች፣ መረጃና በሀገር ውስጥ ምርት የሚደገፍ ሉዓላዊ የጤና ሥርዓት ግንባታን ዋነኛ ራዕይዋ አድርጋ እየሠራች እንደሆነ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0