የአፍሪካ ኅብረት ኬንያዊቷ ፊቢ ኦኮዋ ለዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት መመረጣቸውን አወደሰ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ኅብረት ኬንያዊቷ ፊቢ ኦኮዋ ለዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት መመረጣቸውን አወደሰ
የአፍሪካ ኅብረት ኬንያዊቷ ፊቢ ኦኮዋ ለዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት መመረጣቸውን አወደሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.11.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኅብረት ኬንያዊቷ ፊቢ ኦኮዋ ለዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት መመረጣቸውን አወደሰ 

 

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ የሱፍ በሰጡት መግለጫ የዳኛዋ ዘጠኝ ዓመት የሥራ ዘመን፦ 

 

ለዓለም አቀፍ ሕግ ላደረጉት አስተዋጽኦ የተሰጠ እውቅና፣ 

ለኬንያ እና ለአኀጉሪቱ የኩራት ምንጭ፣

በሕግ ሙያ ለመሰማራት ለሚመኙ አፍሪካውያን ሴቶች እና ወጣቶች ምሥሌ እንደሚሆን ተናግረዋል። 

 

የኦኮዋ የሥራ ዘመን በመጪው የካቲት ይጀምራል። ቀደም ሲል ሶማሊያዊው አብዱልቃዊ የሱፍ ከኃላፊነታቸው ቀድመው መልቀቃቸውን ተከትሎ እ.አ.አ በ2025 እሳቸውን በመተካት በዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ የኬንያ ተወካይ ሆነው ነበር። 

 

ሔግ መቀመጫውን ያደረገው ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት የተመድ ዋና የፍትሕ አካል ነው። ፍርድ ቤቱ በጠቅላላ ጉባኤው እና በደኅንነቱ ምክር ቤት ለዘጠኝ ዓመታት የሥራ ዘመን የሚመረጡ 15 ዳኞችን ያቀፈ ነው። 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0