በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 37 ሰዎች ተገደሉ
17:06 07.11.2026 (የተሻሻለ: 17:14 07.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በምስራቅ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 37 ሰዎች ተገደሉ
የዲሞክራሲ ኃይሎች ጥምረት ታጣቂዎች በሰሜን ኪቩ ግዛት ቤኒ አቅራቢያ በሚገኘው ካንቲን-አሎያ በሰነዘሩት ጥቃት በሲቪሎች ላይ ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ እና የቤት ቃጠሎ ድርጊት መፈጸማቸውን የሀገሪቱን ጦር ጠቅሰው ሚዲያዎች ዘግበዋል።
🪖 ታጣቂዎቹን ለመያዝ ተጨማሪ የጦር ሠራዊት ወደ አካባቢው ተሠማርቷል።
መነሻቸውን ኡጋንዳ ያደረጉት የዲሞክራሲ ኃይሎች ጥምረት ታጣቂዎች፤ በዋነኝነት በምስራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ ከእስላማዊ መንግሥት* የሽብር ድርጅት ጋር ግንኙኘት አላቸው።
*እስላማዊ መንግሥት በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት ነው።
ድህረ ጥቃቱን ያሳያል የተባለ ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኘ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
