ዩክሬን በአፍሪካ የምትሰጠው የድሮን ሥልጠና "አደገኛ ግጭት አባባሽ” እርምጃ እንደሆነ ደቡብ አፍሪካዊው ተንታኝ አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopiaዩክሬን በአፍሪካ የምትሰጠው የድሮን ሥልጠና "አደገኛ ግጭት አባባሽ” እርምጃ እንደሆነ ደቡብ አፍሪካዊው ተንታኝ አስጠነቀቁ
ዩክሬን በአፍሪካ የምትሰጠው የድሮን ሥልጠና አደገኛ ግጭት አባባሽ” እርምጃ እንደሆነ ደቡብ አፍሪካዊው ተንታኝ አስጠነቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.11.2026
ሰብስክራይብ

ዩክሬን በአፍሪካ የምትሰጠው የድሮን ሥልጠና "አደገኛ ግጭት አባባሽ” እርምጃ እንደሆነ ደቡብ አፍሪካዊው ተንታኝ አስጠነቀቁ 

 

ዩክሬን በማሊ የድሮን አብራሪዎችን ማሠልጠንን ጨምሮ በአፍሪካ የምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሩሲያ ጋር መደበኛ ያልሆኑ የግጭት መነሻዎችን ለመፍጠር እና ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ዜወሌቱ ጆሎቤ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። 

 

የተንታኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 

 

🟠 ኢመደበኛ ግጭትን መሣሪያ ማድረግ፦ ኪየቭ ከሩሲያ አጋሮች ጋር በተጻራሪ የቆሙ ወገኖችን በመደገፍ የሞስኮን የደህንነት ትኩረት ለመበታተን በክልላዊ ግጭቶች ውስጥ እጇን ታስገባለች። 

 

🟠 የውጊያ ሜዳውን ማመጣጠን፦ በሳኅል ቀጣና ርካሽ የድሮን ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት ታጣቂ ቡድኖች ትክክለኛ ጥቃት እንዲሰነዝሩ መቻላቸው፤ የአቅም ውስንነት ያለባቸው ብሔራዊ ሠራዊቶች የድሮን መከላከያ ሥርዓቶችን በፍጥነት እንዲታጠቁ ያስገድዳቸዋል። 

 

🟠 የሉዓላዊነት መሸርሸር፦ የአፍሪካ ግዛቶችን ለውክልና ተዋጊዎች መሞከሪያ ማድረግ የአካቢዊውን ነጻነት የሚያኮስስ፣ ማኅበራዊ ልዩነቶችን የሚለጥጥ እና ክልላዊ የሰላም ጥረቶችን ለውጭ አጀንዳዎች የሚሰዋ ነው፡፡  

 

🟠 የሩሲያ አማራጭ፦ ቅድመ ሁኔታ ከሚያስቀምጡ የምዕራባውያን አካሄዶች በተለየ፤ የሩሲያ የደህንነት ትብብር በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተና ሉዓላዊነትን የሚያከብር ነው። 

 

🟠 የወደፊት አቅጣጫ፦ የሳኅል ሀገራት ጥምረት ስትራቴጂያዊ ነጻነታቸውን ለመጠበቅ ጥብቅ የድንበር ቁጥጥር፣ የጠነከረ ክልላዊ የመረጃ ልውውጥ እና ብሔራዊ መከላከያ ኢንዱስትሪን ማሳደግ ቅድሚያ ሊሰጡት ይገባል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0