ሊቢያ እስከ 2032 የሚዘልቅ የድንገተኛ ግዜ የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ እያዘጋጀች ነው - የሀገሪቱ ባለሥልጣን
13:19 07.11.2026 (የተሻሻለ: 13:24 07.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሊቢያ እስከ 2032 የሚዘልቅ የድንገተኛ ግዜ የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ እያዘጋጀች ነው - የሀገሪቱ ባለሥልጣን
ዕቅዱ የ2027 የመንግሥት በጀት እና ከ2027 እስከ 2032 የሚቆይ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ፕሮግራምን እንደሚያካትት የሊቢያ ብሔራዊ የፕላን ምክር ቤት መሪ አህመድ አብሬይዳንለስፑትኒክ ገልጸዋል።
የዕቅዱ ቁልፍ እርምጃዎች፦
◾ በምክር ቤቱ የበላይ ጠባቂነት የሊቢያ የሙህሮች እና ባለሙያዎች ቡድን የኢኮኖሚ ፕሮግራሙን ያዘጋጃሉ።
◾ የበጀት ረቂቁ እስከ ጥር መጀመሪያ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በሕግ አውጪው አካል ጥር ወይም የካቲት 2019 እንዲጸድቅ ታቅዷል።
የሊቢያ ተቀናቃኝ መንግሥታት ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በማለት የኢኮኖሚ ቀውሱን ለመፍታት አብረው ይሠራሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
