ኢትዮጵያ በታሪኳ ከገጠሟት ስብራቶች አንዱ ቀይ ባሕርን ያጣንበት ቀን ነው - የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ
11:52 07.11.2026 (የተሻሻለ: 11:54 07.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በታሪኳ ከገጠሟት ስብራቶች አንዱ ቀይ ባሕርን ያጣንበት ቀን ነው - የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ
ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ይህን ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች እና ፖሊስ ሠራዊት ማኅበራት ኅብረት በኢትዮጵያ የባሕር ወሰን ሕጋዊ ጥያቄ ዙሪያ ባዘጋጀው ሲምፖዘየም ላይ ነው።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ፤ “የኢትዮጵያ እና የቀይ ባሕር ትስስር ሌሎች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረ ክስተት አይደለም። ለሺህ ዘመናት የኖረ ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
"ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ያጣነውን ወደብ እና ያጣነውን የባሕር በር በሕግ፣ በዲፕሎማሲ ካልተሳካም በሌላ በማንኛውም አማራጭ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ያስመልሳል ብለን እናምናለን። ይሳካልም” ብለዋል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች እና ፖሊስ ሠራዊት ኢትየጵያ ለታሪካዊ ጥያቄዋ ምላሽ ታገኝ ዘንድ በትውልዱ ላይ መነሳሳትን እንዲፈጥሩም ጠይቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
