- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት እና የራሽያ-አፍሪካ የትምህርት አጋርነት ሚና

የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት እና የራሽያ-አፍሪካ የትምህርት አጋርነት ሚና
ሰብስክራይብ

"የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ሰንመለከት፣ ለኢንቨስትመንት ላወጡት እያንዳንዱ ዶላር ከኃይል አጠቃቀም ብቻ ሁለት እጥፍ ያህል ተመላሽ ይገኛል። ከዚህም በላይ፣ ያ ኃይል የማዕድን ሃብቶችን እሴት ሰንሰለት ልማት ለማስቀጠል ጥቅም ላይ ከዋለ፣ የኢኮኖሚው ውጤት ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ከመሸጥ እጅግ የላቀ ይሆናል። መጀመርያ ላይ ከፍተኛ ሃብት ማሰማራትን የሚጠይቅ ውሳኔ ወይም ቁርጠኝነት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ወደ ማዕድን ሃብት እሴት ሰንሰለት ልማት ስገቡ ያ ሁሉ ዋጋውን ይከፍላል። የኑክሌር ኃይል በማዕድን ሃብት እሴት ሰንሰለት ልማት ውስጥ እጅግ ማራኪ አማራጭ መሆኑ አያጠራጥርም።"ሲሉ በሞስኮ በሚገኘው የብሔራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ አገራት የኢንዱስትሪ-ትምህርት አጋርነት ፕሮጀክት ኃላፊ ማሳምባ ካህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት ያላቸውን ሚና፣ የማዕድን ሃብት እሴት ሰንሰለት ማሳደግ እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ዕድሎችን እንፈትሻለን። ለዚህም በሞስኮ በሚገኘው ብሔራዊ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ አገራት የኢንዱስትሪ-ትምህርት አጋርነት ፕሮጀክት ኃላፊ ከዶ/ር ማሳምባ ካህ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0