ሩሲያ እና አሜሪካ ለጋራ የሰብዓዊ ሥራዎች ቁርጠኞች ናቸው - ክሬምሊን
15:46 06.11.2026 (የተሻሻለ: 15:54 06.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና አሜሪካ ለጋራ የሰብዓዊ ሥራዎች ቁርጠኞች ናቸው - ክሬምሊን
"...ከሁሉም በላይ ደግሞ አስፈላጊው ነገር ቀናነቱ እና ተመሳሳይ ሰብዓዊ ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ያለው ዝግጁነት ነው" ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
የሩሲያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ያና ላንትራቶቫ የአሌሽኪን ሰብዓዊ ተልዕኮ ለማስፈጸም ከፍተኛ ሥራ ማከናወናቸውን አክለው ገልጸዋል።
የሩሲያ ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪቭ እና የሩሲያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ያና ላንትራቶቫ የሰብዓዊ ተልዕኮው መጠናቀቁን ተከትሎ በኋይት ኃውስ ከአሜሪካ ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ጋር ቀደም ሲል መገናኘታቸው ይታወቃል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
የሩሲያ እና አሜሪካ ሰብዓዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች በሚገባ የሚደጋገፉ ናቸው፣
የሩሲያ እና የዩክሬን የጋራ ደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ ከአውሮፓ ጋር ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ነው፣
የአውሮፓ መሪዎች ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር ማወላወል እና እምቢተኝነታቸው እንደበዛ ተመልከታለች፣
ሩሲያ ስለ አውሮፓ የደህንነት መዋቅር እስካሁን ከአውሮፓ ኀብረት ምንም አይነት ሃሳብ አልደረሳትም፣
ትራምፕ ይፋ ስላደረጉት የሰላም ስምምነት ክሬምሊን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ የለውም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
