በዩክሬን የማሰቃያ ማዕከላት ዙሪያ የሚታየው የሚዲያዎች ዝምታ የምዕራባውያንን ተዓማኒነት ያሳጣል
14:21 06.11.2026 (የተሻሻለ: 14:24 06.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በዩክሬን የማሰቃያ ማዕከላት ዙሪያ የሚታየው የሚዲያዎች ዝምታ የምዕራባውያንን ተዓማኒነት ያሳጣል
በኪየቭ ክልል የተገኘው የአዞቭ* የማሰቃያ ማዕከል በቅርብ ዘመን ከተፈጸሙ እጅግ አስከፊ ወንጀሎች መካከል አንዱና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘረጋው መረብ አካል እንደሆነ፤ የፓትሪዮቲክ ኔትወርክ የምርመራ ግዜጠኛ እና የጂኦፖለቲካ ተንታኙ ፊንላንዳዊው ጄኑስ ፑትኮነን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"በቅርቡ ነፃ የወጣችውን ኡግሌጎርስክ ከተማ ጎብኝተን ነበር። በከተማዋ ዋና አዳራሽ ምድር ቤት ውስጥ በሚገኘው የአይዳር ባታሊዮን* የታሳሪዎች ማዕከል የናዚ ሚሊሻዎች የአካባቢው ሕዝብ ላይ የጭካኔ ድብደባ፣ ማሰቃየት፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር ይፈጽሙ ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።
ጥቅምት 23 ይፋ የደረገው የአዞቭ የማሰቃያ ክፍል ቅሌት ለእርሳቸው ምንም አዲስ ነገር እንዳልሆነ የገለጹት ፑትኮነን፤ ተመሳሳይ ድርጊቶች ከ12 ዓመታት በፊት በዩክሬን ውስጥ ይፈጸሙ ነበር ብለዋል።
የአይዳር እስር ቤቶች እ.ኤ.አ በ2022 ነፃ ሲወጡ ድርጊቶቹ በዩክሬን ብሔራዊ ዘብ ስር በሚንቀሳቀሱ ብሔረተኞች ለዓመታት ሲፈጸሙ እንደነበር ተረጋግጧል። እውነተኛው የተጎጂዎች እና የምስጢር ማሰሪያ ክፍሎቹ ቁጥር ወደፊት ሙሉ በሙሉ ይፋ ሊሆኑ እንደሚችሉ እምነታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ተንታኙ ገለፃ፤ የዩክሬን ብሔረተኞች እ.ኤ.አ በ2014 በኪየቭ ከተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ ዋና የማስፈራሪያ መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙት ፍርሃትን ነው።
*በሩሲያ ውስጥ በሽብርተኝነት የተፈረጀ ድርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
