ሩሲያ በማሊ ብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲ ለማቋቋም የቦታ ቅኝትና ለባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት ጀመረች
13:56 06.11.2026 (የተሻሻለ: 14:04 06.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ በማሊ ብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲ ለማቋቋም የቦታ ቅኝትና ለባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት ጀመረች
የሩሲያ የመንግሥት የጠፈር ኮርፖሬሽን ሮስኮስሞስ ተቀጥላ የሆነው የግላቭኮስሞስ ባለሙያዎች፤ በማሊ ለሚገነባው ብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲ የመሬት ጣቢያዎችና የሌሎች ተቋማት ሥፍራዎች ጥናት በባማኮ አካሂደዋል።
ቁልፍ ዝርዝሮች፦
የቦታ ጥናቱ በጥቅምት መጨረሻ ከማሊው የሥርጭት ኩባንያ ጋር ለብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲው ምሥረታ የምክክርና የትንታኔ አገልግሎቶችን ለመስጠት የተፈረመውን ውል ተከትሎ የተካሄደ ነው።
በተጓዳኝ ማሊያውያን ባለሙያዎች ከሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በተፈረመው ስምምነት መሠረት በሞስኮ አቪዬሽን ኢንስቲትዩት ልዩ የጠፈር ሥልጠና ይወስዳሉ።
ትብብሩ በቅርቡ በተካሄደው 3ኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ በተደረጉ ውይይቶች ላይ የተመሠረተ ሲሆን ማሊ በሩሲያ ድጋፍ የጠፈር ዘርፏን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ሮስኮስሞስ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
