የማሊ እና ኒጄር መሪዎች በፀረ-ሽብርተኝነት እና በሳኅል ጥምረት ትብብር መጠናከር ዙሪያ ተወያዩ
13:45 06.11.2026 (የተሻሻለ: 13:54 06.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የማሊ እና ኒጄር መሪዎች በፀረ-ሽብርተኝነት እና በሳኅል ጥምረት ትብብር መጠናከር ዙሪያ ተወያዩ
የማሊ ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ ከኒጄሩ አቻቸው አብዱራሃማን ቲያኒ ጋር በኒያሜ ሐሙስ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን የሁለቱ ሀገራት የጋራ መግለጫ አመልክቷል።
የስብሰባው ዋና ዋና ውጤቶች፦
ሁለቱ መሪዎች የሳኅል ሀገራት ጥምረት የተቀናጀ ኃይል ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አወድሰዋል።
ኮንፌዴሬሽኑ በክልል፣ በአኅጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠናከር ያስቻሉ የተቀናጁ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን አድንቀዋል።
ሁለቱ ወገኖች የሳኀል ቀጣናን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የደህንነት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።
ከውይይቱ በኋላ ጎይታ ወደ ዋጋዱጉ፣ ቡርኪና ፋሶ አቅንተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
