የዛምቢያ-ታንዛኒያ-ኬንያ የኃይል መስመር ትስስር ከሦስት ዓመታት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ተገለፀ
13:05 06.11.2026 (የተሻሻለ: 13:14 06.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዛምቢያ-ታንዛኒያ-ኬንያ የኃይል መስመር ትስስር ከሦስት ዓመታት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ተገለፀ
ሦስቱን ሀገራት የሚያገናኘው የ2 ሺህ 300 ኪሎ ሜትርና የ1.2 ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛ ቮልቴጅ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2029 ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዛምቢያ የኃይል ሚኒስትር ፒተር ካፓላ መናገራቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል።
▪ ዛምቢያ በ292 ሚሊዮን ዶላር ከ600 ኪሎ ሜትር በላይ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ትገነባለች፣
▪ የኃይል ማስተላለፊያው የደቡባዊ አፍሪካ የኃይል ትስስር እና የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስርን ያገናኛል።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ዛምቢያ እስከ 500 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መገበያየት የምትችል ሲሆን ይህም ቀጣናዊ የኃይል ንግድን የሚያጠናክር እና ሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ንግድ ማዕከል እንደሚያደርጋት ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
