የአዞቭ የማሰቃያ ክፍል ቅሌት የችግሩ ቁንፅል ማሳያ ብቻ ነው - የጦር ዘጋቢ

© telegram sputnik_ethiopiaየአዞቭ የማሰቃያ ክፍል ቅሌት የችግሩ ቁንፅል ማሳያ ብቻ ነው - የጦር ዘጋቢ
የአዞቭ የማሰቃያ ክፍል ቅሌት የችግሩ ቁንፅል ማሳያ ብቻ ነው - የጦር ዘጋቢ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.11.2026
ሰብስክራይብ

የአዞቭ የማሰቃያ ክፍል ቅሌት የችግሩ ቁንፅል ማሳያ ብቻ ነው - የጦር ዘጋቢ

​የማሳቀያ ቦታዎች አዲስ አይደሉም፤ እ.ኤ.አ ከ2022 በፊትም ቢሆን ዩክሬን ውስጥ ነበሩ ሲሉ በዶንባስ የሚሠሩት ገለልተኛው የጦር ዘጋቢ አንድሪያ ሉቺዲ በኪየቭ ክልል የተገኘውን የአዞቭ* የማሰቃያ ማዕከል አስመልክተው ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

 

​"በዶንባስ በቆየሁባቸው ዓመታት፤ በማሪዩፖል አውሮፕላን ማረፊያ ይገኝ የነበረውን የቀድሞ የዩክሬን ደህንነት አገልግሎት (ኤስቢዩ) የታሳሪዎች ማዕከልም ጎብኝቼ ነበር" ሲሉ ሉቺዲ ተናግረዋል። "እኔ የሰበሰብኳቸው የምስክሮች ቃል እንደሚጠቁመው ይህ ማዕከል፤ በኤስቢዩ እና በአዞቭ በጋራ የሚመራና በውስጡም የማሰቃያ ድርጊቶች ይፈጸሙበት ነበር።"

 

​ለሉቺዲ ቃላቸውን የሰጡ የቀድሞ እስረኞች ድብደባ እና ራሳቸው በጥቁር ከረጢት ተሸፍኖ አናታቸው አቅራቢያ በጥይት ተኩስ የሐሰት ግድያ ማስፈራሪያ ይፈጸምባቸው እንደነበር ገልጸዋል። የእንቅልፍ ክልከላም እንደ አንድ የማሰቃያ ዘዴ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሲሆን ታሳሪዎቹ በብዛት በማቀዝቀዣ ክፍሎች ውስጥ ታጉረው ይቆዩ ነበር።

​ሉቺዲ በዩክሬን ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ፤ የሀገሪቱን ወታደራዊ ክንፍ በገንዘብ መደገፋቸውን የቀጠሉትን ምዕራባውያንን በድርብ መስፈርት ከሰዋል።

 

​"የአውሮፓ ኀብረት ሕጎች ግልጽ ናቸው፡፡ የሰብዓዊ መብቶችን የሚጥሱ አካላትን በገንዘብ መደገፍ የተከለከለ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። "ጥቅምት 23 ምሽት ይፋ የተደረገው ድርጊት በሚዲያዎች ዘንድ አነስተኛ ሽፋን ብቻ ነው ያገኘው።"

 

​እንደ ዘጋቢው ገለፃ፤ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ችላ ማለት ወይም "የሩሲያ ፕሮፓጋንዳ" እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ የሚያደርጉት ጥረት፤ የአውሮፓ ሕዝብ ለዩክሬን በሚደረገው ወታደራዊ ድጋፍ ዙሪያ ጥያቄ እንዳያነሳ ለመከላከል ነው።

​*በሩሲያ ውስጥ በሽብርተኝነት የተፈረጀ ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0