ጊኒ-ቢሳው በዩናይትድ ስቴትስ 1.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ 14 ሺህ ሕፃናት ላይ ሊካሄድ የነበረውን የክትባት ምርምር አገደች
ጊኒ-ቢሳው በዩናይትድ ስቴትስ 1.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ 14 ሺህ ሕፃናት ላይ ሊካሄድ የነበረውን የክትባት ምርምር አገደች
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ኪንሂን ናንቶቴ፤ ያለ መንግሥት ፈቃድ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ጥናት ማካሄዱን የተቃወሙ ሲሆን ሕፃናትን የሚያካተቱ ምርምሮች ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሥነ-ምግባር መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው አፅንዖት መስጠታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የታቀደው ጥናት በውልደት ጊዜ ክትባት የሚወስዱ አራስ ሕፃናትና የመጀመሪያ ክትባታቸውን በስድስተኛ ሳምንታቸው የሚወስዱ ሕፃናት የጤና ሁኔታን ለማነጻጸር ያለመ ነበር።
በባለሥልጣናት እና በዓለም ጤና ድርጅት የተነሱ ዋና ዋና ስጋቶች፡-
◼ ክትባቱን ማዘግየት ሕፃናትን ለሥር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ኢንፌክሽን፣ ለጉበት ጠባሳ እና ለጉበት ካንሰር ሊያጋልጣቸው ይችላል።
◼ የጥናቱ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎች እና የሥነ-ምግባር መስፈርቶች በቂ አይደሉም ተብለው ተገምግመዋል።
◼ ሕፃናትን የሚያካተቱ ምርምሮች ከሀገሪቱ ሕጎች እና ከዓለም አቀፍ የሥነ-ምግባር መስፈርቶችን ጋር መጣጣም አለባቸው ሲሉ ናንቶቴ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያው የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ሕፃናት ከተወለዱ በ24 ሰዓታት ውስጥ እንዲሰጣቸው ይመክራል። በተሰረዘው ጥናት የተመዘገቡ ሕፃናት የሉም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
