- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት፣ ታሪካዊ ወዳጅነትና የአፍሪካ ቦታ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም

የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት፣ ታሪካዊ ወዳጅነትና የአፍሪካ ቦታ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም
ሰብስክራይብ
በሞስኮ በተካሄደው 3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ 48 ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን 22ቱ በመሪዎቻቸው ተወክለዋል። ወገኖቹ የጋራ መግለጫ፣ የኤአይ ትብብር ስምምነት እና የ2027 እስከ 2029 የድርጊት መርሃ ግብር አጽድቀዋል።

"ስትራቴጂካዊ ራስን የመቻል መርህ የውጭ አካላትን ፍላጎት ሳይሆን የራስን ብሔራዊ ጥቅም መሠረት አድርጎ የመወሰን ነፃነትና አቅም ነው የሚጠይቀው፤ ይህ ደግሞ አፍሪካ ሁልጊዜ ስትጠይቀውና ሩሲያም ስትደግፈው ለቆየችው የባለብዙ-ዋልታ ዓለም አቀፍ ሥርዓት መሠረት ነው" ሲሉኢትዮጵያዊዉ የሕግ ምሁር አንዷለም በውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሩሲያ ታሪካዊ ትስስሯን [ከአፍሪካ ሀገራት ጋር] መሠረት በማድረግ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚና የደህንነት አጋርነቷን እንዴት እንደምትገነባ እና የእኩልነት፣ የጋራ መከባበርና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት መርሆዎቿ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተግባር ምን ፋይዳ እንዳላቸው ከእንግዳችን አንዷለም በውቀቱ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ህግና ወቅታዊ ጉዳዮች ተንታኝ፣ ጋር በመሆን እንቃኛለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0