አፍሪካ ሴቶች በፖለቲካ አመራር ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅባታል - የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

አፍሪካ ሴቶች በፖለቲካ አመራር ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅባታል - የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

ሁለተኛውን የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ሸዊት ሻንካ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶችን ፖሊቲካዊ ተሳትፎ እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል፡፡

 

“በፖለቲካ አመራር ውስጥ ሴቶች እኩል ድርሻ ሊኖራቸው ይገባል፡፡”

 

ኢትዮጵያ ሴቶች በፖሊሲ ቀረጻ እና ትግበራ እንዲሁም በብሔራዊ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ በእኩልነት እየተሳተፉ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ መፍጠሯን አስረድተዋል፡፡

“የአፍሪካ ትልቁ ስትራቴጂካዊ ሀብት ሕዝቦቿ፣ የፈጠራ አቅማቸው፣ ጽናታቸው እና ቁርጠኝነታቸው ነው። ሴቶች ለተሻለች የወደፊት አፍሪካ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል። ሴቶች በፖለቲካ መሪነት በእኩል የሚወከሉባት፣ በኢኮኖሚ የሚለወጡባት እና መብታቸውን የሚያስጠብቁባት አፍሪካ እውን ልትሆን ይገባል” ብለዋል፡፡

ጉባኤው የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የፓርቲ አመራሮች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ እንደሚገኝ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0