የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ውጥረት ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ውጥረት ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጀመረ
የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ውጥረት ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.11.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ውጥረት ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጀመረ

​የአፍሪካ ኅብረት የአልጀርስ እና የፕሪቶሪያ ስምምነቶች ትግበራን ለማጠናከር ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን የኅብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ገልጸዋል።

​የኅብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የምክክር እና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውንም ይፋ አድረገዋል። ሁኔታው ወደ መጠነ ሰፊ ቀውስ እንዳይቀየር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከሁሉም ወገኖች ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት እንደሚቀጥልም አክለዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ኅበረቱ የጦር መሣሪያ ድምጽ የማጥፋት አጀንዳውን እየገመገመ መሆኑን የገለጹት አዶዬ፤ “የጦር መሣሪያ ድምጽ ማጥፋት ለእኛ መፈክር ብቻ አይደለም። መሪዎቻችን የሰላምን መንገድ ለመከተልና አለመግባባቶችን ወደ ግጭቶች ከመሸጋገራቸው በፊት ለመፍታት የወሰኑት የፍልስፍና አቋም ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0