ዳንጎቴ በናሚቢያ የነዳጅ ማከማቻ እና ቀጣናዊ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አስጀመረ
11:59 05.11.2026 (የተሻሻለ: 12:04 05.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዳንጎቴ በናሚቢያ የነዳጅ ማከማቻ እና ቀጣናዊ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አስጀመረ
የናይጄሪያዊው ቢሊየኔር አሊኮ ዳንጎቴ ኩባንያ በዋልቪስ ቤይ ወደብ የ1.6 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ማከማቻ ፕሮጀክት አስጀምሯል።
የወደቡ የናፍጣ እና የቤንዚን ማከማቻ ታንከሮች 16 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው የማስተላለፊያ መስመር ከወደቡ ጋር የሚገናኙ ሲሆን ዳንጎቴ ኢንዱስትሪስ ተቋሙን ከቦትስዋና፣ ዚምቧቤ፣ ዛምቢያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር የሚያገናኝ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ቀጣናዊ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር የመዘርጋት እቅድ አለው።
"ይህ የነዳጅ ማስተላለፊያ የተወሰኑ የኮንጎ ግዛቶች እና የተወሰኑ የደቡብ አፍሪካ ግዛቶችን በማካተት፤ ለናሚቢያ እና ወደብ አልባ ለሆኑ አጎራባች ሀገራት የነዳጅ አቅርቦት ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለመ ነው" ሲሉ የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋህ በፕሮጀክቱ የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።
የ2.6 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንቱ በሂደት በናሚቢያ የነዳጅ ዋጋን እንደሚቀንስ፤ ቀጣናዊ ማስተላለፊያ መስመሩ ደግሞ በናሚቢያ በኩል ከናይጄሪያ ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጣራ ነዳጅ እንደሚያጓጉዝ አሊኮ ዳንጎቴ ወደ ሀገሪቱ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ፤ በናይጄሪያ በቀን 700 ሺህ በርሜል ነዳጅ የሚያጣራውን ፋብሪካ እንዲሁም በኬንያ ተመሳሳይ አቅም ያለው ፋብሪካ የመገንባት እቅድን ጨምሮ፤ የዳንጎቴ የአፍሪካን የኢነርጂ አቅም የማጎልበት ስትራቴጂ አካል ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
