ኢትዮጵያ እንደ ሕዳሴ ግደብ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም በመገንባቷ ለአፍሪካ ሀገራት ጥሩ አብነት ሆናለች – ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እንደ ሕዳሴ ግደብ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም በመገንባቷ ለአፍሪካ ሀገራት ጥሩ አብነት ሆናለች – ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ

ታንዛኒያ የጁሊየስ ኔሬሬ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብን ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ፋይናንስ እየገነባች ነው ሲሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ኢንጂነር ክፍሌ አክለውም፣ “ይህም የፋይናንስ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት በአካባቢና በማኅበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ላይ የሚያስቀምጧቸው ጥብቅ መስፈርቶች ምክንያት ነው። እነዚህንም መስፈርቶች ድጋፍ ላለመስጠት እንደ ሰበብ ይጠቀሙባቸዋል” ብለዋል።

በተለያዩ የልማት ባንኮች በኩል የሚገኝ ድጋፍ ጠቃሚ ቢሆንም፣ በመቶ በመቶ በእነሱ ላይ ጥገኛ መሆን እንደማይግባም ሥራ አስፍጻሚው ከ36ኛው የአፍሪካ የውሃ ኃይል ሲምፖዚየም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0