የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ዋስትና በኢትዮጵያ፦ ከፖሊሲ ወደ ተግባር፤የአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ
23:19 04.11.2026 (የተሻሻለ: 18:19 13.11.2026)
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ዋስትና በኢትዮጵያ፦ ከፖሊሲ ወደ ተግባር፤የአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ
ሰብስክራይብ
የምግብ ስርዓት የምንለው ከምርት ጀምሮ እያንዳንዱ ሂደት አልፎ ምግብ የሸማቹ አፍ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሰንሰለት ነው።... የአየር ንብረት ለውጥ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ የዕሴት ሰንሰለቱ ላይ ምርታማነትንና ፍጆታን አደጋ ላይ የሚጥሉ መዛባቶችን እየፈጠረ ነው። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ሥርዓት መገንባት ማለት ሥርዓቱ እነዚህን አስደንጋጭ ክስተቶች መቋቋም እንዲችል ማድረግ ነው፤ በዚህም የቤተሰብን ኑሮ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በዘላቂነት ማስቀጠል ይቻላል።" ሲሉ
በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ከዶ/ር ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር ለአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የአፍሪካ ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ፦ ግብርናን ከምርት መጨመር ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም (Resilience)፣ ዘላቂነት እና ሉአላዊነትን ባገናዘበ መልኩ እንዴት እንደገና መቅረፅ እንችላለን? በሚለው ጉዳይ ላይ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ከፍተኛ ተመራማሪ ከሆኑት ከዶ/ር ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር ጋር የምንወያይ ሲሆን፤
👁🗨በክፍል ሁለት፦ የአፍሪካን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ እና ራሷን ከዲጂታል ቅኝ ግዛት ለመታደግ መሰራት ያለባቸውን ሥራዎች የቴክኖልጂ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ባለሙያ ከሆኑት ከዮናስ ገብረሚካኤል ጋር የምንቃኘው ይሆናል፡፡
🔊 ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox