- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የአፍሪካ የልማት ሉዓላዊነት፡ የውስጥ አቅምን ማሰባሰብ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ነፃነት

የአፍሪካ የልማት ሉዓላዊነት፡ የውስጥ አቅምን ማሰባሰብ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ነፃነት
ሰብስክራይብ
የአፍሪካን የግብርና-ምግብ ሥርዓት ከአመራረት ጀምሮ በሙሉ የእሴት ሰንሰለቱ ማዘመን፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ ማምረት እና ከምርት ስብሰባ በኋላ የሚደርሱ ብክነቶችን መቀነስ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሠረት ነው። እነዚህ ሁሉ ሂደቶች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ ሲሆን፣ መፍትሔው የታወቀ ቢሆንም አሁን የሚያስፈልገው ትክክለኛ መሬት ላይ ያለ ተግባራዊ እርምጃ ነው።

"የግብርና-ምግብሥርዓታችንን ከአመራረት ጀምሮ በሙሉ የእሴት ሰንሰለቱ ማዘመን አለብን። ምርታማነትን ማሳደግ አለብን። ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ ማምረት አለብን። ከምርት ስብሰባ በኋላ የሚደርሱ ብክነቶችን መቀነስ አለብን። እናም ይህ ሁሉ ኢንቨስትመንትን ይፈልጋል። ምንም ነገር በነጻ የሚመጣ የለም። መፍትሔውን እናውቀዋለን፤ የጎደለን ነገር ቢኖር እርምጃ ነው። መሬት ላይ ያለ ተግባራዊ እርምጃ።" ሲሉ የዓለምየምግብና ግብርና ድርጅት ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ አበበኃይለ-ገብርኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነት፣ የግብርና-ምግብ ሥርዓት ማሻሻያዎችን እና መሬት ላይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ተግባራዊ እርምጃዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የዓለም የምግብና ግብርና ድርጅት ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ ከሆኑት ከአበበ ኃይለ-ገብርኤል ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0