ዴሞክራቶች የአሜሪካን ኮንግረስ መቆጣጠራቸው "በዓለም አቀፍ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ያመጣል" - የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት
20:44 04.11.2026 (የተሻሻለ: 20:54 04.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዴሞክራቶች የአሜሪካን ኮንግረስ መቆጣጠራቸው "በዓለም አቀፍ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ያመጣል" - የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በደቡብ አፍሪካ የአካባቢ አስተዳደር ምርጫ ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ውጤቶች ለውጦችን ያመጣሉ።
"ከአሜሪካ ጋር ሁልጊዜም ጥሩ ግንኙነት ለመመሥረት ፈቃደኞች ነን... ነገር ግን እኛም እንደ እነርሱ ሉዓላዊ ሀገር ነን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ደቡብ አፍሪካ የራሷን ጥቅም እንደምታስከብር አክለው ገልጸዋል።
ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ እድገት እና ዕድል ሕግ (አጎዋ) መታገዷን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት ራማፎሳ፣ ድርጊቱን "ለእኛ አሉታዊ ጎን ያለው ነው" ያሉት ሲሆን "በአህጉራችን ላይ የሚገኙ በርካታ ሀገራትም በተመሳሳይ ከሕጉ ተገለዋል" ሲሉ ጠቁመዋል።
ይሁንእንጂ፣ ደቡብ አፍሪካ የውጭ ንግድ ገበያዎቿን ያሰፋች በመሆኑ፣ ኩባንያዎቿም "ከበርካታ ሌሎች ሀገራት ጋር ሥራ ጀምረዋል" ሲሉ አብራርተዋል።
"የገበያ አማራጮችን ማስፋፋት አሁን ላይ የዕለት ተዕለት አቅጣጫ ሆኗል።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
